Property Law

Property Law (27)

Ethiopian Property Law is the system of laws relating and prioritizing the rights, interest and responsibilities of individual in relation to things. These things are a form of property or right to possession or ownership of an object. This section will provide you property law related articles. 

ይህ ዓይነት የአእምሮ ንብረት መብት ለኢትዮጵያ አዲስና ከወጣም ብዙ ዓመታትን ያላስቆጠረ መብት ነው፡፡ የዕፀዋት አዳቃዮች መብት ለማስጠበቅ የወጣው አዋጅ ቁጥር 481/98 አላማም በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ ተመራማሪዎችና በልማዳዊ አሰራር ዝርያን የሚያዳቅሉ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች የሰራቸው ውጤት ተጠቃሚዎች ለመሆን የሚያስችላቸውን ኢኮኖሢያዊ ጥቅም ለማስጠበቅና የቆየው የዝርያ መጠቀምና መለዋወጥ ልማዳዊ ስርዓታቸው እንዲቀጥል ለማድረግና…
የንግድ ምልክት ማለት ምን ማለት እንደሆነ የንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 501/98 በአንቀፅ 2(12) ላይ፡- የንግድ ምልክት ማለት የአንድን ሰው ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች ከሌሎች ሰዎች ወይም አገልግሎቶች ለመለየት የሚያስችል የሚታይ ምስል ነው፡፡ ምልክቱ ቃላቶችን፣ ዲዛይኖችን፣ ፊደሎችን፣ ቁጥሮችን፣ ቀለሞችን ወይም የዕቃዎችን ወይም የመያዣዎቻቸውን ቅርፅ ወይም የእነዚህኑ ቅንጅት ሊይዝ ይችላል፡፡ በማለት…
የቅጅና ተዛማጅ መብቶችን በማስመልከት የወጣው አዋጅ ቁጥር 410/96 በአንቀፅ 2(8) ላይ "የቅጅ መብት ማለት ከአንድ ስራ የሚመነጭ የኢኮኖሚ መብት ሲሆን አግባብነት ባለው ጊዜ የሞራል መብቶችን ይጨምራል" በማለት ሲተረጉመው ተዛማጅ መብት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ደግሞ በአንቀፅ 2(14) ላይ " ተዛማጅ መብት ማለት ከዋኝ፣ የድምፅ ሪከርዲንግ ፕሮዲሰር፣ የብሮድካስቲንግ ድርጅት በስራው ላይ…
ህገ-መንግስታዊ መሰረቱ የአእምሮ ንብረት ከድሮ ጀምሮ ሮማውያን የግለሰብ መብት (personal right) እና ግዙፍ መብት (real right) በሚል ከሚመድቧቸው የንብረት መብቶች በተጨማሪ ለየት ያለ መብት ሲሆን ስያሜውን በተመለከተ የተለያዩ ፀሓፍት የተለያየ አጠራር ሲጠቀሙ ይስተዋላል:: ለዚህም አንዳንዶቹ ግዙፍነት የሌለው መብት (incorporeal right)  ሌሎቹ ደግሞ የአእምሮ ንብረት (inteiiectual property) በማለት ይጠሩታል:: ይህ ግን…
የምዝገባ አላማዎች   በኢትዮጵያ የፍ/ብሄር ፍትህ ስርዓት የማይንቀሳቀስ ንብረት ምዝገባ በዜጎች የንብረት መብት ጥበቃ ፋይዳው የጎላ ቢሆንም እምብዛም ፍታብሄር ህጉ በሚደነግገው መሰረት ሲሰራበት አይታይም:: የማይንቀሳቀስ ንብረት ምዝገባን በማስመልከት የተለያዩ አገሮች የተለያየ አሰራር ይከተላሉ:: ለምሳሌ ፈረንሳይ transcription የሚባለውን እሰራር ስትከተል አውስትራልያ matriculation የሚባለውን አሰራር ትከተላለች:: በአገራችን ያለው የማይንቀሳቀስ ንብረት ምዝገባ ስር’ዓትም…
ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ከይዞታው የሚለቅ ሰው በቅድሚያ ተመጣጣኝ ካሳ የማግኘት መብት ሕገ- መንግስታዊ መብት ነው፡፡ የዚህን የህገ-መንግስቱ አንቀጽ 40(8) መርህ ተግባራዊ ለማድረግ የወጣው አዋጅ ቁጥር 455/97 በአንቀጽ 7 ላይ የካሳ መሰረትና መጠን በሚል ርእስ ስርና በአንቀጽ 8 ላይ የማፈናቀያ ካሳ በሚል ስር ሁለት ዓይነት የካሳ ክፍያዎች እንዳሉ በሚገልጽ መልኩ ተደንግጓል፡፡…
ህገ መንግስታዊ  መስረቱ የኢ ፌ.ዲ.ሪ  ህገ - መንግስት የመሬት ባለይዞታነትን በማስመልከት  ቀደም ሲል ለመዳሰስ እንደተሞከረው በአንቀፅ 40 እና 89(5) ላይ ዜጉች በገጠርን ሆነ በከተማ መሬት አጠቃቀም ስለሚኖሩዋቸው መብቶችና ግዴታዎች እንዲሁም አስተዳደሩን በማስመልከት የመሬት ባለቤትና የመንግስትና የህዝብ መሆኑን በእርግጠኛነት የሚደነግግ መሆኑን እያየን መጥተናል፡፡ አሁን ከያዝነው ርእስ ጉዳዩ አኳያም አንቀፅ 40(8) ላይ…
ህገ-መንግስታዊ መሰረቱ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ-መንግስት የገጠር መሬት ባለይዞታነትን መብት መሰረት በማድረግ አጅግ በርካታ ለሆኑ የንብረት መሰረታዊ መብቶች እውቅና የሰጠ ነው ፡፡ በአገራችን ለአመታት የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀምን መሰረት በማድረግ እዚህም እዚያም ይነሱና ለግጭት መንስኤ በመሆን ዜጎች እርስ በርሳቸው ደም እንዲቃቡ ያደርጉ የነበሩትን ችግሮች በሚቀርፍ መንገድ መልስ የሰጠና በህዝብ ይሁንታ ያገኘ የፖሎቲካና…
ህገ-መንግስታዊ መሰረቱ መንግስት በህገ-መንግስቱ ለህዝብ የገባቸውን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ግዴታዎች ለመፈፀም ደግሞ የግድ በይዞታው ስር አድርጐ የሚያዝበት መሬት ሊኖረው ይገባል፡፡ ለምን ቢባል መንግስት ያለ እንደዚህ ያለ የኢኮኖሚ መሳርያ ዘላቂ ልማት፣ ዲሞክራሲ፣ መልካም አስተዳደርና የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ጠንካራ ኢትዮጵያን ሊገንባ አይችልም፡፡ ስለሆነም ይህን ይሁለንተናዊ ዘላቂ የልማት መሰረት የሆነውን መሬት በመንግስት…
አገራችን ኢትዮጵያ አሁን እየተከተለችው ባለ ህገ-መንግስታዊ ስርዓት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 8(1) “የኢትዮጵያ ብሄር-ብሄረሰቦች ህዝቦች የኢትዮጵያ ልኡላዊ ስልጣን ባለቤቶች ናቸው፡፡” በማለት የሚደነግግ ሲሆን የህገ-መንግስቱ አንቀፅ 40(3) እንደዚሁ ከንብረት ባለቤትነት መብት አንፃር “የገጠርም ሆነ የከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሀብት ባለቤትነት መብት የመንግስትና የህዝብ ብቻ ነው፡፡ መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች የጋራ…
የንብረት አገልግሎት ስለ ሌላ የማይንቀሳቀስ ንብረት ጥቅም በአንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚጣል ግዴታ ነው፡፡ (ፍ/ብ/ህ/ቁ. 1359) የንብረት አገልግሎት መሰረቱ (subject matter) የማይንቀሳቀስ ንብረት ሲሆን የመብቱ ምንጮች (sources) ህግ፣ ውልና ተፈጥራዊ አቀማመጥ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የንብረት አገልግሎት መብት ቀደም ሲል እንደ አላባ መብት በሚንቀሳቀሱ ንብረቶችና ግዙፍነት በሌላቸው እንደ ፈጠራ፣ የቅጅ መብትና፣ የኢንዱስትሪ…
የአላባ መብት ከአንድ ግዙፍነት ያለው የሚንቀሳቀስ ወይም የማይንቀሳቀስ ንብረት ወይም ግዙፍነት ከሌለው የባለቤትነት መብት ተቀንሶ በንብረቱ ለመገልገል (usus) ወይም ፍሬውን የመሰብሰብና መውሰድ (fructus) መብት በመስጠት የሚቋቋም የንብረት ግንኙነት ነው፡፡ ይሄውም አንድ ሰው ካለው የባለቤትነት መብት ቀንሶ ለሌላ ሰው የሚያስተላልፈው መብት ነው፡፡  አንድን ንብረት በአላባ የማስተላለፍ መብት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ…
ሁለተኛው የጋራ ባለሃብትነት ግንኙነት ልዩ የጋራ ባለሃብትነት ሲሆን የዚህ መብት መሰረት (subject matter) የጋራ ግንብ፤ አጥር፡ አፓርትማ ወ.ዘ.ተ. ሊሆን ይችላል፡፡ (ፍ/ብ/ህ/ቁ.1209(1)) ሰዎች በዚህ ዙርያ የሚኖራቸውን መብት በማስመልከት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 40(7) ማንኛወም ኢትዮጵያዊ በጉልበቱ ወይም ለሚያደርገው ቋሚ ንብረት ወይም ለሚያደርገው ቋሚ መሻሻል ሙሉ መብት አለው፡፡ . . ."  በማለት ሁለት…
የጋራ ባለሃብትነት ምንድን ነው? የጋራ ባለሃብትነት መብት በመሰረቱ በሁለት እና ከዚያ በላይ በሆኑ ሰዎች መካከል በሚደረግ ውል የሚቋቋምና የሚገዛ የጋራ ንብረት ባለሃብትነት መብት ወይም ከህግ በሚመነጭ የጋራ ባለሃብትነት የሚቋቋም የንብረት መብት ነው፡፡ የጋራ ባለሃብትነት መብት ከፍታብሄር ህግ አኳያ ሲታይ በሁለት ማለትም ተራ የጋራ ባለሃብትነት (Ordinary joint ownership) እና ልዩ የጋራ…
Page 1 of 2