ይህ ሀላፊነት በእንግሊዝኛው /vicarious liability/ የሚባለው ነው፡፡ የተደነገገውም ከ2124 እስክ 2136 ባሉት ቁጥሮች ስር ነው፡፡ ሀላፊነትን የሚያስከትለው ተግባር የተፈፀመው በአንዱ ሰው ሲሆን ተጠያቂ የሚሆነው ግን ሌላ ሰው ነው፡፡ ሀላፊነት የሚያስከትለውን ተግባር የሚያከናውኑት ሦስት ዓይነት ሰዎች ናቸው፡፡ እነሱም አካለ መጠን ያላደረሰ ልጅ፣ ሠራተኛ እና ደራሲያን /ፀሐፊዎች/ /authors/ ናቸው፡፡ ሠራተኛ የሚለው የመንግስት…