Employment and Labor Law

Employment and Labor Law (17)

Labour or Employment law in Ethiopia is applied to such matters as employment, remuneration, conditions of work and trade unions. In addition to the individual contractual relationships growing out of the traditional employment situation, Labour or Employment law deals with the various rights and obligations.

 

የመብት ጥያቄ የሚቀርብበት ጊዜና ዓላማው በደል የደረሰበት ሰው በደሉን ለሚመለከተው አካል አቅርቦ ለማሰማት ያለው ዕድል በጊዜ የተገደበ ነው፡፡ የጊዜው ርዝማኔ መጠን እንደየአገሩ፣ በጉዳዩ ውስጥ እንዳለው የመብት ዓይነት ሊለያይ ይችላል፡፡ ከንብረት መብት ጋር በተያያዘ፣ ከውል ውጭ በደረሰ ጉዳት ምክንያት ወይም ከወንጀል ድርጊቶች የተነሣ የሚቀርቡ ጥያቄዎች የየራሳቸው የይርጋ ጊዜ ተቀምጦላቸዋል፡፡ በተወሰነው የጊዜ…
ትርጉም ቃሉ በአሠሪና ሠራተኛ መካከል ያለ አለመግባባትን ይጠቁማል፡፡ በአሠሪና ሠራተኛ ህጉ አዋጅ ቁጥር 136(3) ላይ በተሰጠው ትርጉም የሥራ ክርክር ማለት ሕግን፣ የኀብረት ሥምምነትን፤ የሥራ ደንብን፣ የሥራ ውልን፣ ወይም ሲሠራበት የቆየ ልምድን መሠረት በማድረግ እንዲሁም በኀብረት ስምምነት ወቅት ወይም ከኀብረት ስምምነት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በሚመለከት በአሠሪና ሠራተኛ ወይም በሠራተኞች ማኀበር እና…
የሥራ ውል ተዋዋይ ወገኖች አቅዋም ሲመዘን አንድ ዓይነት የድርድር አቅም ሊኖራቸው እንደማይችል ይገመታል፡፡ አሠሪው ከሠራተኛው የኢኮኖሚ አቅም ይልቅ በተሻለ ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡ ይኸው ጥንካሬም በውሉ ስምምነት ጊዜ ሊያንፀባርቅ ይችላል፡፡ አሠሪው ሠራተኛውን ከሚፈልገው በላይ ሠራተኛው ሥራውን ይፈልጋል፡፡ በዚህ የተነሣም ተቀጣሪው ሠራተኛ በአሠሪው ፈቃድ ስር እንዲሆን ሁኔታዎች ያስገድዱታል፡፡ አሠሪው ቢኢኮኖሚው ጥንካሬ ምክንያት…
መግቢያ አንድ አሠሪ በየትኛውም ሁኔታና ዋጋ ቢሆን ከፍ ያለ ትርፍ የማግኘት ፍላጐት አለው፡፡ ሠራተኛው በሌላ በኩል ሰብዓዊ ክብሩና የሥራ ደህንነቱ ተጠብቆ የሚሠራበት ጊዜና ሁኔታ ተመቻችቶለት ለጉልበቱ ተገቢ የሆነ ክፍያ እንዲያገኝ ይፈልጋል፡፡ እኒህ ተቃራኒ የሆኑ ፍላጐቶች በአሠሪውና በሠራተኛው መካከል አለመግባባትን የመፍጠር ኃይል ያላቸው ሲሆን ችግሩን በመፍታት ረገድ ሁሉም ወገን ያሻውን እንዲያደርግ…
በልዩ ግዴታ ምክንያት የሚሰጡ አገልግሎቶች የስራ ጉዳት በደረሰ ጊዜ አሠሪው ልዩ ግዴታዎች አሉበት፡፡ ይኸውም በጊዜው የህክምና ዕርዳታ መሥጠት ተስማሚ በሆነ የመጓጓዣ ዘዴ በአቅራቢያው ወደሚገኘው የህክምና ጣቢያ ማድረስ እና የሠራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የሥራ ላይ ጉዳት መድረሱን ማሳወቅ እንዲሁም ጉዳቱ እንዲሁም ጉዳቱ ሞትን ባስከተለ ጊዜ የቀብር…
የአካል ጉዳት መጠን ደረጃዎች የአካል ጉዳት መጠን ደረጃዎች በአራት ይከፈላሉ፡፡ ይኸውም ጊዜያዊ የአካል ጉዳት ዘላቂ ከፊል የአካል ጉዳት ዘላቂ ሙሉ የአካል ጉዳት እና ሞት ናቸው፡፡ እንደየቅደም ተከተላቸው በሚከተለው ሁኔታ እናያቸዋለን፡፡ ሀ. ጊዜያዊ የአካል ጉዳት፡- የዚህ ጉዳት ሰለባ የሆነ ሠራተኛ የተመደበበትን ሥራ ለተወሰነ ጊዜ በሙሉ ወይም በከፊል ለማከናወን እንዳይችል ይሆናል አንቀጽ…
ትርጉም   በሥራ ምክንያት የሚመጣ በሽታን ትርጉም ማወቅ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ከበሽታዎች ውስጥ የትኛው በስራ ምክንያት እንደሚመጣ የትኞቹ ደግሞ በተለመደው ሁኔታ የሰውን ልጅ የሚያጠቁ  ከሥራ ጋር ያልተያያዙ እንደሆኑ ለመለየት ይረዳል፡፡ በኢትዮጵያ አሠሪና ሠራተኛ ህግ መሠረት በሥራምክንያት የሚመጣ በሽታ ማለት   “ሠራተኛው ከሚሠራው የሥራ ዓይነት ወይም ሠራተኛው ከሚያከናውነው ሥራ አካባቢ የተነሣ…
በሥራ ሂደት ወይም ከሥራ ጋር በተያያዘ ሁኔታ በማናቸውም ጊዜ ያልታሰቡ አደጋዎች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ በተለይም ዘመናዊው የኢንዱስትሪ አሠራር ሂደት እያደገና እየተወሳሰበ መምጣቱ ከመሥሪያዎቹ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ አደጋ የመፈጠር ዕድሉን ሠፊ ያደርገዋል፡፡ ከድኅነት ጋር ተያይዞም ችግሩ ይከፋል፡፡ ጉዳቱም ከተጎጂው ዘልቆ በሥሩ የሚተዳደሩ ቤተሰቦቹን የሚነካ በመሆኑ ከፍ ያለ ቀውስን በህብረተሰቡ ውስጥ የሚፈጥር ነው፡፡ …
በስራ ግንኙነት ውስጥ የአሰሪና ሰራተኛ ህግ አስፈላጊነት ከሚገልጹ ምክንያቶች ውስጥ በአንድ በኩል ሰራተኛውን አግባብ ካልሆነ ብዝበዛ መከላከል በሌላ በኩል ደግሞ ሰራተኛው የሚፈለግበትን ግዴታዎች በአግባቡ እንዲወጣ ማደረግ የሚገኙበት መሆኑን ቀደም ብለን ያየነው ነው፡፡ ለዚህም ከሌሎች በተጨማሪ ሕጉ ዝቅተኛ የስራ ሰዓትን ፣ የዕረፍት ጊዜን እና የፈቃድ ጊዜ አሰጣጥን በመወሰን ይቆጣጠራል፡፡ በዚህ መልኩ…
የስራ ውል የሚቋረጥባቸው ምክንያቶች የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት ሙሉ በሙሉ ለተዋዋይ ወገኞች ፈቃድ ብቻ እንዳይተውና ህግ ጣልቃ እንዲገባ ከሚያደርጉ ሁኔታዎች ውስጥ አንዱ ከስራ ውል መቋረጥ ጋር የተያያዘ ምክንያት ነው፡፡ ሥለዚህም የስራ ውል በዘፈቀደ ሳይሆን በበቂ ምክንያቶች ላይ ተመስርቶ የተቋረጠ መሆኑን ለማረጋገጥ ሕግ አስፈላጊውን ጥበቃ ያደርጋል፡፡ ይህን የሕግ ጥበቃ ተግባራዊ ለማድረግ በተለያዩ…
በስራ ውል የተፈጠረው የአሰሪና ሰራተኛ የስራ ግንኙነት በሚቀጥለው ክፍል ውስጥ እንደምንመለከተው ለዘለቄታው ሊቋረጥ እንደሚችል ሁሉ ለጊዜውም ሊታገድ ይችላል፡፡ የውሉ መታገድ ከስራ ውል መቋረጥ በመለስ ለጊዚያዊ አገልግሎት የሚደረግ የመብትና ግዴታዎች መታገድ ቢሆንም እገዳው እስከቆየበት ጊዜ ድረስ ሰራተኛው ስራውን የመስራት ግዴታ አሰሪው ደግሞ በህብረት ስምምነት መሰረት በሌላ አካኋን ካልተወሰነ በስተቀር ደሞዝና ሌሎች…
በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 መሠረት የአሰሪው እና የሰራተኛው ጠቅላላ ግዴታዎች በሁለት አንቀጾች ስር ተካተው ይገኛሉ፡፡ በዚህም መሰረት አንቀጽ 12 የአሰሪውን አንቀጽ 13 ደግሞ የሰራተኛውን ግዴታዎች ይዘረዝራሉ፡፡ ከነዚህም በተጨማሪ ከአዋጁ አንቀጽ 12/8/ እና 13/7/ መረዳት እንደሚቻለው ሰራተኛው በህግ የሚኖረውን መብት እስካላጠበቡ ድረስ የስራ ውል፣ የሕብረት ስምምነትና የስራ ደንብ እንደ ሁኔታው…
አሰሪና ሰራተኛ ህግ በርካታ ጥቅሞች የሚኖሩት ሲሆን ጠቅለል ተደርገው በሶስት ዋና ዋና ርእሶች ስር ተከፍለው ሊታዩ ይችላሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ የሰራተኛውን ጥቅም ማስከበር ወይም ሰራተኛውን ከአሰሪው አግባብ ያልሆነ ጥቃቶች እና ብዝበዛ መከላከል ቀዳሚው የህጉ ፋይዳ ሲሆን የስራ ግንኙነቱን የሚመለከቱ ህገመንግስታዊ ድንጋጌዎች በተግባር እንዲውሉ ማድረግ እና ኢንቨስትመንትን በማሳለጥ ለእኮኖሚያዊ እድገት እና ልማት…
ትርጉም የአሰሪና ሠራተኛ ህግ በመሰረቱ በአሰሪና በሰራተኛ መካከል በሚደረግ የስራ ውል ላይ ተመስርቶ የሚፈጠሩ ግንኙነቶችን የሚመራ፣ የሚቆጣጠር ህግ ነው ተብሎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አሰሪ እና ሠራተኛ የሚሉት ስያሜዎች ሲታዩ ጠቅለል ያሉ ስያሜዎች ስለሆኑ እንደየሁኔታው የተለያዩ ሕጎችን የሚጠቁሙ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አንድ ወገን አሠሪ ሌላኛው ወገን ደግሞ ሠራተኛ ሊሆኑበት የሚችሉ በርካታ ዘርፎች ሲኖሩ…
Page 1 of 2