ለፌዴራል መጀመሪያና እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለዕጩ ዳኝነት ለቃል ፈተና ያለፉ ተወዳዳሪዎች ይፋ ሆነ

Nov 26 2015

 

ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና ለፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ርድ ቤት በዕጩ ዳኝነት ከተወዳደሩት ውስጥ ለቀጣዩ የቃል ፈተና ያለፉ ተወዳዳሪዎች ይፋ ሆነ፡፡ የቃል ፈተናው ሕዳር 18 እና 19 ቀን 2008 ዓ.ም እንደሚሰጥም ታውቋል፡፡ የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ሕፈት ቤት እንደገለፀው ቀደም ሲል በተሰጠው የጽሑፍ ፈተና የተሻለ ውጤት ያመጡ ተወዳዳሪዎች ለቃል ፈተና እንዲቀርቡ በተሰጣቸው መለያ ቁጥር /ኮድ/ መሠረት ዝርዝራቸው ይፋ ተደርጓል፡፡

በዚሁ መሠረት ለፌዴራል ከፍተኛ ርድ ቤት ዕጩ ዳኝነት ከቀረቡት ሴት ተወዳዳሪዎች መካከል 60 እና 60 በላይ ያመጡ 15 ተወዳዳሪዎት ለቃል ፈተና ያለፉ ሲሆን በተመሳሳይ ለፌዴራል ከፍተኛ ርድ ቤት ዕጩ ዳኝነት ከቀረቡ ወንድ ተወዳዳሪዎች መካከል 70 እና 70 በላይ ውጤት ያመጡ 29 ወንድ ተወዳዳሪዎች ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸው ተረጋግጧል፡፡ በተመሳሳይ ለፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዕጩ ዳኝነት ከቀረቡት ሴት ተወዳዳሪዎች መካከል 70 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡ 51 ሴት ተወዳዳሪዎች ከወንድ ተወዳዳሪዎች መካከል ደግሞ 80 እና ከዚያ በላይ ያመጡ 76 ወንድ ተወዳዳሪዎች ለቃል ፈተና ማለፋቸው ይፋ ተደርጓል፡፡

ለቃል ፈተና ያለፉ ተወዳዳሪዎችን በተመለከተ መረጃ ፈላጊዎች በዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ጽሕፈት ቤት ስልክ ቁጥር 0111 56 56 84 ወይም 011156 56 85 በመደወል መረጃ ማግኘት እንደሚችሉ ሕፈት ቤቱ አስታውቋል፡፡

 

ውጤትዎን ለማወቅ ይህችን ተጭነው ያውርዱ 

Read 42462 times Last modified on Nov 26 2015
Abyssinia Law | Making Law Accessible!

Abyssinia Law is  a legal resource portal providing open access to primary and secondary legal materials for Ethiopia, such as laws, court decisions, articles, contact guidance and Lawyers Directory - with texts supplemented by online videos, a discussion forum and user blog. The service gives free access to Federal and State consolidated laws of Ethiopia (with status information whether the law is amended, repealed or effective)