በጋምቤላ፤ በአማራ ተወላጆች ላይ ጉዳት ያደረሱ ሹማምንት ተከሰሱ

Sep 25 2015

በጋምቤላ ክልል በተለይም በአማራ ተወላጆችን (ደገኞች) ኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ በማፈናቀልና በመግደል ወንጀል የተጠረጠሩ 46 የቀድሞ የክልሉ ሹማምንት ክስ ሰሞኑን በአዲስአበባ የፌዴራል ከፍተኛ ርድ ቤት ተረኛ ችሎት ቀረበ። ከቀበሌ እስከ ዞን በአመራርነት ርከን ነበሩ የተባሉት ተከሳሾች ባቀጣጠሉት ግጭት 126 ሰዎች በግፍ የተገደሉ ሲሆን ሺህ የሚልቁ ሰዎችን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል።

የፌደራል ዓቃቤ ሕግ 2006 እና 2007 .ደገኞች ከክልላችን ይውጡልንበሚል በጋምቤላ ክልል ማዣንግ ዞን፣ ጎደሬ እና ሜጢ እንዲሁም በሌሎችም ቀበሌዎች የወንጀል ፈጽመዋል ባላቸውና ከቀበሌ እስከ ዞን በአመራርነት እርከን፣ በሚሊሻነት እና በተለያዩ የግል ሥራ የተሰማሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር በማዋል ክስ መስርቷል።

ዓቃቤ ሕግ ተከሳሾች ዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን ዜጎችን በማስታጠቅ አንዱ በሌላው ላይ የጦር መሣሪያ እንዲያነሳ አነሳስተዋል የሚለቱን ወንጀል ሕግ አንቀጾችን ጠቅሶባቸዋል። በተጨማሪም የእርስ በእርስ ግጭት እንዲነሳሳ ለማድረግ በመስማማት፣ በማደም  በወንጀል ድርጊቱ ተሳትፈዋል ብሏል።

 

 

Read 41686 times
Abyssinia Law | Making Law Accessible!

Abyssinia Law is  a legal resource portal providing open access to primary and secondary legal materials for Ethiopia, such as laws, court decisions, articles, contact guidance and Lawyers Directory - with texts supplemented by online videos, a discussion forum and user blog. The service gives free access to Federal and State consolidated laws of Ethiopia (with status information whether the law is amended, repealed or effective)