ጦማሪ አቤል ዋበላ የእስራት ቅጣት ተፈረደበት

Jun 04 2015

በሽብር ወንጀል ተከሰው በክርክር ሒደት ላይ ከሚገኙት ጦማሪያን መካከል አንዱ የሆነው ጦማሪ አቤል ዋቤላ ፍርድ ቤት በመድፈር ወንጀል ጥፋተኛ በመባል በአራት ወራት እስራት እንዲቀጣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19 ወንጀል ችሎት ወሰነ፡፡ ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ አቤል ዋቤላ በተከሰሰበት ወንጀል ክርክር ሂደት መልካም ጸባይ እንዳሳየ በመግለጽ የአራት ወራት እስራቱን በሁለት ዓመታት ገድቦለታል፡፡

 

ጦማሪ አቤል ይህ ውሳኔ የተወሰነበት ግንቦት 19 ቀን 2007 ዓ.ም ዓቃቤ ሕግ በተከሳሾቹ ላይ አዲስ ሲዲ ባቀረበበት ወቅት የቀረበው ሲዲ የሚመለከተው ሶሊያና ሽመልስን ብቻ ነው? ወይስ እኛንም ያካትታል?” የሚል ጥያቄ አቅርቦ ፍርድ ቤቱ እንዳይናገር ሲከለክለው በመናገሩና ፍርድ ቤቱን ‹‹ራሳችሁ ሥነ ሥርዓት›› በማለት  ኃይለ ቃል ተናግሯል በሚል ነው፡፡

Read 46075 times
Abyssinia Law | Making Law Accessible!

Abyssinia Law is  a legal resource portal providing open access to primary and secondary legal materials for Ethiopia, such as laws, court decisions, articles, contact guidance and Lawyers Directory - with texts supplemented by online videos, a discussion forum and user blog. The service gives free access to Federal and State consolidated laws of Ethiopia (with status information whether the law is amended, repealed or effective)