በዚህ ክፍል አንድን ጉዳይ አስመልክቶ ከወጡ ሕጎች (ድንጋጌዎች) መካከል ከሕጉ ዓላማ፣ የሕጉ አፈፃፀም እያደረሠ ካለው ችግር፣ ከሕጉ ኋላ ቀርነት፣ ከሌሎች ሀገራት ተሞክሮዎችና ሌሎች ነጥቦች አንፃር ተጨባጭና ምክንያታዊ መከራከሪያዎችን በማንሳት ሊሻሻሉ ይገባል የምንላቸውን ድንጋጌዎች እንዳስሳለን፡፡ የዚህ ክፍል ዓላማ ለሕግ አውጪው ሊሻሻሉ የሚገባቸውን የህግ ድንጋጌዎች (ሕጎች) ከነምክንያታቸው ማመላከትና የሚሻሻሉበትን ሁኔታ መጠቆም ነው፡፡