በዚህ ክፍል አንድን ችግር ለመፍታት ወይም አንድን ድርጊት ለመቆጣጠር ከወጡ ሕጎች መካከል ሕጉ በሚፈልገው መጠን ያልተተገበሩ የሕግ ድንጋጌዎችን እንዲሁም ዝርዝራቸው በሕግ ይወሰናል ተብሎ ያልተወሰኑ ድንጋጌዎችን እንዳስሳለን፡፡ የዚህ ክፍል ዓላማ ለኅብረተሰቡ፣ ለሕግ አውጪው፣ ለሕግ አስፈጻሚው እና ለሕግ ተርጓሚው እየተሠራባቸው ስላልሆኑ የሕግ ድንጋጌዎች በማሳወቅ ድንጋጌዎቹ ወደ ተግባር የሚቀየሩበትን መንገድ ማመላከት ነው፡፡